
#4ኛው_ሀገር_አቀፍ_የክህሎት_ውድድር የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።
“ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ዛሬ በይፍ ተጀምሯል፡፡
የማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከሚያዝያ 27-ግንቦት 2/2017 ዓ.ም ሲሆን ውድድሩ ለስድስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል፡፡
ውድድሩ በአሰልጣኝ፣ በሰልጣኝና በኢንተርፕራይዝ ምድብ ተከፍሎ የሚካሄድ ከውድድሩ ጎን ለጎን የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበትና የሚሸጡበት ኤግዚቢሽን ነው፡፡
የክህሎት ውድድሩ በሰልጣኞች ምድብ በ22 የሙያ መስኮች የሚካሄድ ሲሆን አሰልጣኞች በቴክኖሎጂና በተግባራዊ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ኢንተርፕራይዞች በቴክኖሎጂ ውድድር ይሳተፋሉ፡፡
ኮሌጃችን በዚሁ ኢትዮ-ክህሎት የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ ውድድር ላይ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ይዞ የቀረበና እንዲሁም በኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ የተሰሩ የአትክልትና ፍራፍሬ፤ የጨው ምርቶቻችንን ጨምሮ ለ6 ተከታታይ ቀናትን የሚያስተዋውቁበት መድረክ ይሆናል፡፡
ሚያዝያ 27/2017 ዓ.ም


