
ቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ከስልጠና በላይ…
(Entrepreneurial TVT)
ላለፍት 3 አመት ከግማሽ የዘርፍን ሪፎርም በ 4 ምሰሶ በ38 ኢኒሽየቲቮች ላይ ተመስርተን እያካሄድን እንገኛለን:: ከ38 አስራ አንድ የሚሆኑት በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ እየተካሄዱ ያሉ ናቸው:: ከነዚህ መካከል የ 5 ቱ የፌደራል ግብርና ኮሌጆች ተጠቃሽ ነው::
ከ 5ቱ የግብርና ኮሌጆች አንዱ የሆነው የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚገኝ ሲሆን ከሥልጠና በላይ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት እያደረገ ያለውን ጥረት በሀገራችን በጨው ምርት ከሚታወቁ አካባቢዎች አንዱ በሆነው አፋር ዶቢ በመገኘት ተመልክተናል፡፡ ከግብርና ኮሌጆች ቦርድ አመራሮች ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል፡፡
በዘርፉ በመተግበር ላይ የሚገኘው ሪፎርም ተቋሞቻችን ከመማር ማስተማር ተልዕኳቸው ባሻገር አካባቢያዊ ፀጋዎቻቸውን ለይተው በማልማት፣ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን በማላመድና በማሸጋገር እንደየ ተልዕኳቸው የልህቀት ማዕከል እንዲሆኑ ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡
በሁሉም ተቋማት የተጀማመሩ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ ናቸው:: አዳዲስ ምርት በየአካባቢው ማስተዋወቅ ችለዋል:: አዲስ ሀብት ፈጥረዋል:: ቢሆኑም ካላቸው እምቅ አቅም አንፃር ብዙ መስራትን ይጠይቃል፡፡
አሁን ላይ ተቋሞቻችን ከሰርቶ ማሳያነት ያለፈ ሜካናይዝድ እርሻን፣ ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን ለማስፋት አልመው እየሠሩ ይገኛል፡፡
በእስካሁኑ ሂደት ለተገኙ ውጤቶች ከችግሮች በላይ ሆኖ ለሪፎርሙ ስኬት በየደረጃው የሚገኘው የአማካሪዎች ቡድን፣የቦርድ አባላቱ፣ አመራርና ባለሙያ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ
የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ዑመር ኑር እና ከፍተኛ አመራሮች ላደረጋችሁልን ደማቅ አቀባበል ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
ነሀሴ 10/2017 ዓ.ም
የኮሌጁ የህዝብ ግኑኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ
#ለወቅታዊናትኩስመረጃ፦
👉Web. www.gewanetvt.edu.et
👉Telegram https://t.me/grwanecommunicationaffairs
👉Facebook፦ https://www.facebook.com/profile @.php?id=100076472559939
👉Tik Tok .https://vm.tiktok.com/ZMM7bUjRd