የ ኮሌጅ ዲን መልዕክት መሀመድ ሀመዱየገዋኔ ግብርና ኮሌጅ ዲን ክቡራን የኮሌጃችን ተመራቂዎች እንካን ደስ አላችሁ!! ከሁሉ አስቀድሜ በኮሌጃችን ላለፉት ሶስት አመታት በኮሌጃችን ትምህርታችሁን በመከታተል አስፈላጊውን መመዘኛዎችን በማለፍ በደረጃ 4 ለምትመረቁ ተማሪዎቻችን እንካን ደስ አላችሁ ለማለት እፈልጋለሁ$ ውድ የኮሌጃን ተመራቂ ተማሪዎች!!...
Dean of Message
የ ኮሌጅ ዲን መልዕክት
ክቡራን የኮሌጃችን ተመራቂዎች እንካን ደስ አላችሁ!!
ከሁሉ አስቀድሜ በኮሌጃችን ላለፉት ሶስት አመታት በኮሌጃችን ትምህርታችሁን በመከታተል አስፈላጊውን መመዘኛዎችን በማለፍ በደረጃ 4 ለምትመረቁ ተማሪዎቻችን እንካን ደስ አላችሁ ለማለት እፈልጋለሁ$
ውድ የኮሌጃን ተመራቂ ተማሪዎች!!
ኮሌጃችን በዛሬው እለት የገዋኔ ግብርና ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ለ18ኛ ጊዜ በጠቅላላው ከ 170 በላይ ተማሪዎችን በደረጃ 4 በሰብል ልማት፤በእንስሳት ልማት፤እና በአካባቢ ጥበቃ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ያስመርቃል $
ለዛሬው የምረቃት ቀን እንድትደርሱ በጣም በርካታ አካላት ያላሰለሰ ጥረትና ድጋፍ በመሆኑ በቅድምያ ለተማሪቂ ቤተሰቦች የዛሬው ቀን የናንተም ድካምና ልፋት በመሆኑ እንካን ደስ አላችሁ ለማለት እፈልጋለሁ በመቀጠል እናንተን ለማብቃት ቀን ከለሊት ላለፉት ሶስት አመታት ሲጥሩ ለነበሩት መምህራን የልፋታችሁን ውጤት በማየታችሁ መምህራኖቻችን እንካን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ$
በመቀጠል እናንተ ውድ ተማሪዎቻችን የናንተ ውድ ጊዜያችሁን ለትምህረታችሁ በመስጠት በብዙ ችግሮችን ተቛቁማችሁ ኮሌጃችን በአንዳንድ አገልግሎት ውስነነቶችንም ታግሳችሁ አላማችሁን በማሰብ ለዛሬው እለት ሰለበቃቸሁ በድጋሚ እንካን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ$
ውድ ተማሪዎቻችን
ተመራቂ ተማሪዎቻችን ላስገነዝባችሁ የምፈልገው ነገር ቢኖር በዛሬው እለት ተመረቃችሁ ማለት ትምህርት አለቀ ማለት ሳይሆን የመጀመሪያ ምዕራፍ እንደጀመራችሁና በቀጣይ ትምህረታቸሁን በማሻሻል ራሳችሁን የበለጠ ማብቃት ይጠበቃል ሆኖም ግን በተማራችሁ የትምህርት ዘርፍ ደግሞ ሳይማር ያስተማራችሁን ማህበረሰብ በ አፈርና ውሃ ጥበቃ በሰብል ልማት በእንስሳት እርባታ የቀሰማችሁትን ትምህርት በመጠቀም ህዛባችሁን በማስተማር ዘመናዊ የእርሸ ስራና የእንስሳት እርባታን እንዲከተሉ በማስቻል በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉ ብሎም ወደ ገበያ ምርታቸውን እንዲያወጡ መንግሰታችን ለያዘው እቅድ የናንት የዛሬ ተመራቂዎቻችን ከፍተኛ ሚና እንደሚጠበቅ ለማስታወስ እወደለሁ$
በመጨረሻም በኮሌጃችን ላለፉት 3 አመታት በሰብል ልማት፤በእንስሳት ልማት እና በአካባቢ ጥበቃ ሳይንስ የንድፈ ሀሳብና የተግባር ትምህርታችሁን በበቂ ሁኔታ ተከታትላችሁ በዛሬው እለት ለተመረቃችሁ ተማሪዎቻችን በቀሰማችሁት እውቀት ከስራ ተቀጣሪነት ወደ ስራ ፈጣሪነት አመለካከት በማተኮር በማህበረሰባችሁ እና በራሳችሁ ህይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ እንደምታመጡ በመተማመን በቀጣይ ጊዜ መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማችሁ እየተመኘሁ በድጋሚ እንካን ደስ አላችሁ ለማለት እወደላሁ$
መሀመድ ሀመዱ
የገዋኔ ግብርና ኮሌጅ ዲን