
#አፍር_ዶቢ_ገዋኔ_ግብርና_ኮሌጅ በዶቢ የጨው ምርት ደርሶ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።
****************,****************************************************
የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ከመማር ማስተማር ባሻገር የክልሉን ፀጋ በመጠቀም ቀደም ሲል ከአፍር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከመአድን ቢሮ በዶቢ የጨው መምረቻ ቦታ ፍቃድ አግኝቶ ወደ ስራ በፍጥነት ተሰማርቶ በመግባት የጨው ምርቱ ዛሬ ላይ ፍሬ አፍርቶ መሰብሰብ ደረጃ ደርሷል ሲሉ የኮሌጁ ዲን ክቡር አቶ መሀመድ ሀመዱ ገልፀዋል።
አክለውም በኮሌጃችን የገቢ ምንጫችንን ለማሳደግ አሁን ላይ እያመረተ ከሚገኘው የጨው ምርት በቀጣይ የማምረቻ ጊዜ በእጥፍ የማምረቻ ቦታዎችን በማስፍፍት የኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ ተልዕኳችንን ለማስፈፀም የጎላ ሚና አለው ብለዋል።
የኮሌጁ የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ ም/ዲን አቶ ዳንኤል ስለሺ በኮሌጁ በኢንተርፕራይዝ ዘርፍ 2017 ዓ.ም የተለያዩ የገቢ ምንጭ የሚያስገኙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን በመግለፅ ዛሬ ላይ በዶቢ በመገኘት የተመረተውን የጨው ምርት ገበያ ላይ እንዲውል አስፈላጊውን ሂደቶች በአፍጣኝ እየተከናወኑ መሆናቸውንና በቅርቡ የመጀመሪያው ዙር የጨው ምርት ስራዎች እንደሚጠናቀቁና ወደ ቀጣይ ዙር የማምረት ሂደት እንደሚገባ አሳወቁ።
በመጨረሻም የኮሌጁ ዲን ለፌድራል ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መ/ቤት፣ለአፍር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና ለክልሉ ማዕድን ቢሮ ፣ለክልሉ ባለሀብት አስ መሀመድ እንዲሁም ለዚሁ ውጤት መሳካት በየደረጀ የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡ የኮሌጁ አመራሮች ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
ሰኔ 16/2017 ዓ.ም


