የገዋኔ_ግብርና ቴ/ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ ከLLRP (የቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት) ጋር በሠመራ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

የገዋኔ_ግብርና ቴ/ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ ከLLRP (የቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት) ጋር በሠመራ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
………………………………
የኮሌጁ ዲን ክቡር አቶ መሀመድ ሀመዱ በዛሬው ዕለት በአጫጭር ስልጠና ወጣቶችን የራሳቸውን የስራ እድል መፍጠር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ LLRP (ከቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት) አስተባባሪ ክቡር አቶ መሀመድ ሀሰን ጋር በውቢቷ ሠመራ ከተማ በዋና መስሪያ ቤት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ክቡር አቶ መሀመድ ሀሰን ሥልጠናው በንብ ማነብ/ Bee keeping / ከተለያዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ በጋራ ፍላጎት ላይ ለሚሰማሩ ማህበራት የሚሰጥ እና ከሥልጠናው ቡሀላ ለበቁበት ስልጠና አስፈላጊውን ግብዓት ተሟልቶ የራሳቸው የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸው ወደ ስራ እንደሚገቡ እንዲሁም በቅርቡ ስልጠናው በገዋኔ ግብርና ኮሌጁ እንደሚሰጥ ተገለጿል።
በመጨረሻም የኮሌጁ ዲን አክለውም ይህ በዛሬዋ ዕለት የተደረገው ስምምነት ከእንደዚህ ቀደሙ የተሰጠንን ኃላፊነት እንደተወጣነው ሁሉ አሁንም ሰልጣኞችን በሚላኩልን የሙያ መስክ በተግባር የተደገፈ ስልጠና እንዲሁም በክህሎት የበቁ ዜጎችን ለራሳቸው የስራ ዕድልን ለመፍጠር የሚያስችል ስልጠናን ለመስጠት ኮሌጁ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው ሰልጣኞችን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *