
#20ኛው_ዙር_የሰልጣኞች_ምረቃ_ሥነ_ስርዓት_በገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ ተደርጎ ውሏል።
******************************************************
በዛሬው ዕለት የምረቃ ሥነ-ስርዓት ላይ ክቡር አቶ ጌታቸው ደምሴ በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የግብርና ቴ/ሙያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ፤ክቡር አቶ መሀመድ ሀመዱ የኮሌጁ ዲን ፤ክቡር አቶ ግርማ ለገሰ የሚዛን ግብርና ኮሌጅ አስተዳደር ዘርፍ ም/ዲን ፤ክቡር አቶ አህመድ ኢብራሂም የአፍር ብ/ክ/ መንግስት የሥራና ክህሎት ሚኒስተቴር ኃላፊ፣ክቡር አቶ አባሀባ ሁሴን የገቢ-ረሱ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች፣መምህራንና ሰራተኛች፣የአካባቢ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣የፀጥታ ዘርፍ እና የዕለቱ ተመራቂ ሰልጣኞች በተገኙበት ተክብሮ ዉሏል።
ኮሌጁ በሶስት አመት ቋይታቸው ሲሰለጥኑ የቆዩትን በእንስሳት ሳይንስ፣በእፅዋት ሳይንስ እና በተፈጥሮ ሀብት 361 ሰልጣኞችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ሚያዝያ 30/2017 ዓ.ም


