#በሥራና_ክህሎት_ሚኒስተር ተጠሪ 5ቱ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጆች የ2017 የግማሽ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ።
…………………………………… ………………………..
ግምገማው ክብርት ወ/ሮ ሙፍሪሃት ካሚል በተገኙበት በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የኮሌጃችንን የ2017 የግማሽ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፓርቱን የኮሌጁ ዲን ክቡር አቶ መሀመድ ሀመዱ ቀርቧል ።
በቀረበው ሪፖርት ላይ በተሰጠው አስተያየት ኮሌጁ በመማር ማስተማር በገቢ ራሱን ለመቻል እና ዲጂታላይዝ በማድረግ ላይ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በተለይ ራሰ አገዝ ለመሆን በዶቢ የጀመረው የጨው ማምረቻ በአጭር ጊዜ ወደ ውጤት መቀየሩ በጣም የሚበረታታ መሆኑን ኮሌጁ በኢንተርፕራይዝ ልማት የመማር ማስተማር ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት የበለጠ ለመከወን እንደ ማስፈንጠሪያ ሊያገለግል ይችላል ተብሏል።
በተጨመሪም በክብርት ሚ/ር የተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ኮሌጁ በገጠር ወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ በምርቶች ላይ እሴት ሰንሰለት መጨመር፣በእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ማህበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች እንዲሰሩ እና የተጀመረው የሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው ተግባራዊ እንዲደረጉ አሳስበዋል።
የካቲት 26/2017 ዓ.ም
#የኮሌጁ_የህዝብ_ግኑኝነትና_ኮሙዩኒኬሽን_ሥራ_አስፈፃሚ
#ለወቅታዊናትኩስመረጃ፦
👉Web. www.gewanetvt.edu.et
👉Telegram https://t.me/grwanecommunicationaffairs
👉Facebook፦ https://www.facebook.com/profile @.php?id=100076472559939
👉Tik Tok .https://vm.tiktok.com/ZMM7