በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ “የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ስራዎች የተዘጋጁ ሰነዶችን” ለኮሌጁ መምህራንና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በሪፎርም ኮሚቴዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄድ ።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን ክቡር አቶ መሀመድ ሀመዱ ጊዜያቸውንና የተሰጣቸውን ኃላፊነት ደከመን ሰለቸን ሳይሉ እየሰሩ ላሉት ለሪፎርም ቴክኒካል ኮሚቴዎች ላቅ ያለ ምስጋና ካቀረቡ ቡሀላ የኮሌጁ ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እንዲተገበሩ ገምግመው ባፀደቁት ዕቅድና ሰነዶች መሠረት ሥራዎች እንዲተገበሩ አቅጣጫ የሰጡበት መድረክ ነው።
ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዋነኛ አላማው ሰራተኞች ስለ ሪፎርም ግንዛቤ እንዲኖራቸው ኮሚቴው በሰባቱ የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም  አምዶች እንዲሁም ጠቅለል ብለው በተደራጁት አራት ምድቦች ማለትም:-
> የፖሊሲና የህግ ማሻሻያ ሥራዎች
> የአደረጃጀት ማሻሻያ ሥራዎች
> የብቃት ማዕቀፍ ማሻሻያ ሥራዎች
> የአገልግሎትና ማሻሻያ ሥራዎች ምድቦች የተሰሩ ሰነዶችና እቅዶች ላይ በስፍት የተዳሰሰበትና ለሰራተኞች ጠለቅ ያለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ዕድልን የፈጠረ መድረክ  ሲሆን በቀጣይ ሁሉም ዕቅዶችና ሰነዶች ፀድቀው ለሚመለከታቸው ክፍሎችና ስራ አስፈጻሚዎች እንደሚላኩና በፀደቀው ሰነድ መሰረት ሥራዎች መሰራት እንዳለባቸውና ሪፎርሙን መቀበል መቻል እንጂ አለመቀበል አይቻልም ሲሉ የገለፁት ክቡር አቶ ሰመሊ መሀመድ የአስተዳደር ዘርፍ ም/ዲን እና የሪፎርም ኮሚቴ ሰብሳቢ በጥብቅ አስታውቀዋል።

ታህሳስ 20/2017 ዓ.ም
የኮሌጁ የህዝብ ግኑኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ

#ለወቅታዊናትኩስመረጃ፦
👉Web. www.gewanetvt.edu.et
👉Telegram https://t.me/grwanecommunicationaffairs
👉Facebook፦ https://www.facebook.com/profile @.php?id=100076472559939
👉Tik Tok .https://vm.tiktok.com/ZMM7bUjRd

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *