#የገዋኔግብርናኮሌጅየ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ነባር የሁለተኛና የሶስተኛ ዓመት ተማሪዎችን ህዳር 12 እስከ 14 /2017 ዓ.ም ቅበላ አደረገ።

********
ቀደም ሲል የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሁለተኛና የሶስተኛ ዓመት ሰልጣኞችን ለመቀበል ባወጣው የጥሪ ማስታወቂያ መሠረት ሰልጣኛች ወደጊቢ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
ይህንኑ አስመልክቶ የኮሌጁ መምህራንና ሥራ አስፈፃሚዎች ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአዲስ መንፈስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን የሚያስችላቸውንና ለአሰልጣኞችና ሥራ አስፈፃሚ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የጋራ ፕሮግራም አዘጋጅተዋል።

በፕሮግራሙ የኮሌጁ ወኪል ዲን አቶ ሰለሞን በቀለ፣የኮሌጁ የሥልጠና ዘርፍ ም/ዲን አቶ አንተነህ ሽፈራው እና የቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ ም/ዲን አቶ ዳንኤል ስለሺ በተገኙበት መድረክ የተለያዩ ዝግጅቶች የተካሄደበትና የ2017 ዓ.ም የት/ት ጊዜ በአዲስ መንፈስ ጥሩና ውጤታማ የሆነ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር መነሳሳትን የፈጠረ መድረክ መሆኑን የመድረኩ ተካፍዮች ገልፀዋል።
ህዳር 15/2017 ዓ.ም
የኮሌጁ የህዝብ ግኑኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *