የኮሌጁ ዲን ክቡር አቶ መሀመድ ሀመዱ የተመራ ከፍተኛ አመራሮች የልዑካን ቡድን የ2017 ዓ.ም የምርት ዘመን በአጋርፍ ግብርና ኮሌጅ በመገኘት ስምምነታቸውን አደድሰዋል።
ቀደም ሲል 2016 ዓ.ም የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ከአጋርፍ ግብርና ኮሌጅ ጋር በተደረገው የሁለትዩሽ ስምምነት ኮሌጁ 300 ሄክታር መሬትን በመረከብ በ100 ሄክታር መሬት ላይ ምርት በመሰብሰብ 1912357.65(አንድ ሚሊየን ዘጠኝ መቶ ሺህ ሶስት መቶ ሀምሳ ሰባት ብር ከ ስልሳ ሳንታም) ለኮሌጁ ገቢ መደረጉን ተከትሎ በ2017 ዓ.ም ከመሰከረም 19-21, 2017 ዓ.ም የኮሌጁ ዲን ክቡር አቶ መሀመድ ሀመዱ የተመራ ከፍተኛ አመራሮች የልዑካን ቡድን በአጋርፍ ግብርና ኮሌጅ ቁይታቸውን አድርገዋል ።
በተደረሰው ገቢን በጋራ ከማሳደግ አኳያ ዘርፈ ብዙ ስምምነት መሠረት የ2017 ዓ.ም የምርት ዘመን 300 ሄክታር መሬት ላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ አሁን ላይ በተለያዩ የተፈጥሮ ምክንያቶች ማለትም ከፍተኛ በሆነ የክረምት ዝናብ በሁሉም ሄክታር ላይ ማፍሰስ ባለመቻሉ በ100 ሄክታር ላይ የፈሰሰውን የገብስ እርሻን ሁኔታ በመስክ በመገኘት ግምገማ በማድረግ እና ከማነጀመንቱ ጋር በቀጣይ ጉንኝነታችን እና ምርታማነት ሰለማሻሻል እንዲሁም በቀሪው 200 ሄክታሩ መሬት ላይ ከየካቲት ወር ስራዎች እንደሚቀጥሉ ስምምነት ላይ በመድረስ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን
በመስክ የታየው የሰብል ሁኔታ መልካም መሆኑና ከባለፈው የተሻለ ምርት የሚጠበቅ መሆኑንና ውይይቱም ፊሬያማ እንደነበር ክቡር የኮሌጁ ዲን አቶ መሀመድ ሀመዱ ገልፀዋል።
መስከረም 23/2017 ዓ.ም
የኮሌጁ የህዝብ ግኑኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ
ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ፦
Web. www.gewanetvt.edu.et
Telegram https://t.me/grwanecommunicationaffairs
Facebook https://www.facebook.com/profile @.php?id=100076472559939
Tik Tok .https://vm.tiktok.com/ZMM7bUjRd