የገዋኔ ግብርና ቴ/ሙያ ኮሌጅ ለአማአሳቡሪ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2017 የትምህርት ዘመን ወላጆቻቸው በአነስተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
…………………………………………..
በስነ-ሥርአቱ ላይ የኮሌጁ አስተዳደር ዘርፍ ም/ዲን የሆኑት አቶ ሰመሊ መሀመድ ፣የኮሌጁ የአንድ ቀን ለህዝቤ ማህበራዊ ድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አራጋው ተሰማ ፣ የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ ኢናሀባ አሊ፣ የት/ት ቤቱ ክላስተር ሱፐርቫይዘር አቶ ሁሴን አበበ፣የት/ት ቤቱ ርዕሰ መምህር መ/ር አማረ ብርሃን እንዲሁም የት/ት ቤቱ የወላጆች ኮሚቴ በተገኙበት የተደረገ ሲሆን፦
የገዋኔ ግብርና ቴ/ሙያ ኮሌጅ ከኮሌጁ ሰራተኞች ከወር ደመወዛቸው አንድ ፐርሰንት(1%) በማሰባሰብ አንድ ቀን ለህዝቤ በሚል ርዕስ ኮሚቴ አቋቅሞ በጊዜዊ ድጋፍና በቋሚነት በቁጥር 21 አቅመ ደካማ የአካባቢ ማህበረሰቦችን በመለየት ያለማቋረጥ በየወሩ ድጋፍ በማድረግ 6አመታት ያስቆጠረ ሲሆን በዛሬዋ ዕለትም በኮሌጁ አካባቢ ለሚገኘው ለአማአሳቡሪ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ወላጆቻቸው በአነስተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 45 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ የተገኘነው ሲሉ የኮሌጁ አስተዳደር ዘርፍ ም/ዲን የሆኑት አቶ ሰመሊ መሀመድ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ኮሚቴው ከኮሚቴነት ባለፍ በሚመለከተው አካል እውቅና ተሰጥቶት በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ለሚገኙና አቅመ ደካማዎችን በስፍት የሚያቅፍ የበጎ ፍቃድ ማህበር እንዲሆን ከመቼውም ባለፈ ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል።
መስከረም 21/2016 ዓ.ም
የኮሌጁ የህዝብ ግኑኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ
ለወቅታዊና ትኩስ መረጃ፦
Web. www.gewanetvt.edu.et
Telegram https://t.me/grwanecommunicationaffairs
Facebook https://www.facebook.com/profile @.php?id=100076472559939
Tik Tok .https://vm.tiktok.com/ZMM7bUjRd