የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እህት ኮሌጅ ከሆነው ከአጋርፍ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ጋር ቀደም ሲል በተደረጉው የሁለትዮሽ የጋራ ስምምነት መሰረት ከአጋርፍ ግ/ቴ/ሙያ ኮሌጅ 300 ሄክታር የእርሻ መሬት ርክክብ ተደረገ ።

ኮሌጃችን 2016 ዓ.ም 15 ሚሊየን በውስጥ ገቢ ማስገኘት እንዳለበት ከሚኒስተር መ/ቤት አቅጣጫ መሰጠቱ ይታወቃል ። ይህንኑ ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ ኮሌጁ የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ ከመቼውም በላይ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል ። የኮሌጁ ሉዑካን ቡድን በአጋርፍ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በመገኘት ቀደም ሲል የጋራ የሆነ የሁለትዮሽ ስምምነት በተደረገው መሰረት 300 ሄክታር የእርሻ መሬት ርክክብ በማድረግ በጋራ አብሮ ለመስራትና ለማደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳዩበት ነው ።

የአጋርፍ ቴ/ሙያ ኮሌጅ ዲን የተከበሩ ዶ/ ር ጫላ ፈየረ ይህ ከእህት ኮሌጅ ከገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ጋር ያደረግነው ስምምነት በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በዘመናዊ እንስስሳት እርባታ፣ በእርሻ መሬቶች እና በማሽነሪ ትውውስ በጋራ በትብብር በመደጋገፍ በጋራ ለመስራት የተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት ነው ሲሉ አብራርተዋል።
በመቀጠልም በያዝነው ዕቅድ እስከ ሀምሌ 2015 ዓ.ም ከተረከቡት 300 ሄክታር መሬት ላይ ኮሌጃችን በራሱ ሙሉ ወጪውን ተሸፍኖ በ100 ሄክታር መሬት ላይም ገብስ ለመዝራት ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉን እና በቅርብ ክትትል እስከ ምርት ማምረት ክትትል ተደርጓ ገቢው በተደረገው ስምምነት መሰረት ለገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እንደሚደረግ የአጋርፍ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ብዜትና ሽግግር ም/ዲን ፍራኦል ኤዶን ገለፁ።

የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲን ክቡር አቶ መሀመድ ሀመዱ ኮሌጁ ለአጋርፍ ኮሌጅ ስምምነቱን አስመልክቶ ባደረጉት የሁለትዮሽ የልማት ስምምነት ደስታ የፍጠረባቸው መሆኑን እንዲሁም በጋራ በመስራትና በመደጋገፍ ፤ በቀጣይ አመታት በተረከቡት በ300 ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ የተለያዩ ልማትን በኮሌጁ ወጪ ተሸፍኖና ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ አሳወቁ።

የኮሌጁ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ሚያዝያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *