የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የደረጃ 4 ተማሪዎችን አስመረቀ

የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የደረጃ 4 ተማሪዎችን አስመረቀ
..
የገዋኔ ግ/ቴ/ ሙያ ኮሌጅ ቀደም ሲል ከአላጌ ግ/ቴ/ ሙያ ኮሌጅ 1 ዓመት ተምረው ወደ ኮሌጃችን  በሀገራዊ ጉዳይ ዝውውር የተደረገላቸውን 182 የእንሳት ሳይንስ ሰልጣኝ ተማሪዎችን በኮሌጁ ከ2 አመት ቆይታ ቡሀላ አስመረቀ።
በዕለቱ የፌድራል ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የቴክኒክና ሙያ ከፍተኛ አመራሮች፣የኮሌጁ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች እንዲሁም የአካባቢ ማህበረሰቦች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል ።
በስራና ክህሎት ሚኒስተር የግብርና ቴክኒክና ሙያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ጌታቸው ደምሴ ከሚንስተር መ/ቤቱ  በቀጣይ አመታት ኮሌጁ ከ level 4 ወደ level 5 በማሳደግ የትምህርት አሰጣጡ እንደሚያድግም በዚሁ የምረቃ ፕሮግራም ላይ ለኮሌጁ አበስረው ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የክቡር የኮሌጁ ዲን አቶ መሀመድ ሀመዱ  መልዕክታቸውን በእንኳን ደስ አላችሁ ከፍተው በመቀጠል እንዲህ ብለዋል ውድ የዛሬዋ ቀን ተመራቂዎች ለዛሬ ምርቃት ያበቃችሁ የትላንት ትጋታችሁ እና ልፍታችሁ እንዲሁም የመምህራናችሁ ጥረት ተደምሮ ነው ካሉ ቡሃላ ለተመራቂ ተማሪዎቻቸው በመጨረሻም ከዚህ ተመርቃችሁ ወደ ማህበረሰባችሁ ስትቀላቀሉ በእንስሳት ዘርፍ በመሰማራት ስራን በመፍጠር ሀገራችንን በእንስሳት ዘርፉ የላቀ ውጤት እንድታመጣ የእያንዳንዳችሁ በ3 ዓመት ቆይታችሁ የተማራችሁትን ትምህርት ወደ መሬት በማውረድ ስራ ፈጣሪ ወጣት በመሆን የተሰጣችሁን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት እራሳችሁን፣ ቤተሰቦቻችሁን ፣አካባቢያችሁንና ሀገራችሁን በእንስሳት ዘርፍ የላቀ ውጤት እንድታመጣ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል
ሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም
የኮሌጁ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *