የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መምህራን ለዓመታት የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ሲጠይቁ ቆይተው ይሄው ከብዙ ውጣ ዉረዶች ቡሃላ መፍትሄ አግኝቶ በአዋሽ 7ኪሎ ከተማ ለአጠቃላይ መምህራን እያንዳንዱ 300 ካሬ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደረሰኛቸውን የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።
በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ የመምህራን የብዙ ጊዜ ጥያቂያቸው መፍትሄ አግኝቶ ማየታቸውን ተከትሎ የተሰማቸውን ታላቅ ደስታ ገልፀዋል።
የኮሌጁ ዲን ክቡር አቶ መሀመድ ሀመዱ በተሰጣቸው ቦታ ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታቸውን ለመጀመር ያስችላቸው ዘንድ ከአዋሽ ባንክ ጋር ኮሌጁ ስምምነት ማድረጉን እና የብድር አገልግሎት እንደተመቻችላቸውም ሲያበስሩ ድርብ ደስታን ፈጥሮላቸዋል።
የኮሌጁ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም