በሀገሬ ምርት እኮራለሁ ፤ ከሀገር ውስጥ አምራቾች እገዛለሁ”ኤግዚቢሽን እና ባዛር በሐዋሳ ከተማ በይፋ ተከፈተ ።
የገዋኔ ግብርና ቴክኔክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከግብርና ሚኒስቴር እና ከሲዳማ ብ/ክ/መንግስት የሥራ፣ ክህሎት እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ ከ246 ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎታቸውን በሚያቀርቡበት ዝግጅት ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል ።
ኤግዚቢሽን እና ባዛሩ ላይ ምርታቸውን የሚሸጡበት ብቻ ሳይሆን ኢንተርፕራይዞች ልምድ፣ የሥራ ባህል እና ቴክኖሎጂ የሚጋሩበት የባዛር ዝግጅት ሲሆን ኮሌጃችን በባዛር ዝግጅቱ በኮሌጃችን እየተከናወኑ ያሉ ምርጥ ችግር ፈች ቴክኖሎጂዎችን፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን እና ፈጠራዎችን በማቅረብ ተሳታፊ ሆኗል ።
ይህ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከተቋቋመ በኋላ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተደረገ የመጀመሪያው ባዛር መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይም በተለያዩ ክልሎች እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በአዲሱ እሳቤ በመመራት ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን ሸጠው አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ እና ለሌሎችም የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ያስችላል ብለዋል።
በመጨረሻም ኤግዚቢሽን እና ባዛሩ ከጥር 4 – 9 2015 ዓ.ም የሚቆይና የ6 ሚሊዮን ብር ግብይት እንደሚፈፀምበት እና ከ35 ሺህ በላይ ህዝብ እንደሚጎበኘውም ይጠበቃል ።
የኮሌጁ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት