የገዋኔ ግብርና ቴ/ሙ/ሥ/ኮሌጅ ከቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በአትክልትና ፍራፍሬ፣ወተት ተዋፅኦ፣በእንስሳትዋና መድሀኒት አገልግሎት እና በዶሮ እርባታ በአራት ዘርፍ ለተደራጁ ማህበራት የተሰጠ የአጫጭር ጊዜ ስልጠና የምረቃ ፕሮግራም ተካሄደ።
ታህሳስ -16- 2015 ዓ.ም
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች ፣የክልሉ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ዋና ሀላፊዎች፣ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ፣ከተለያዩ አካባቢ የመጡ የክብር እንግዶች እና የኮሌጁ የፕሮጀክቱ አስፈፃሚ ሀላፊዎችና አሰልጣኝ መምህራን በተገኙበት የምረቃ ፕሮግራም ተካሂዷል።