በገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የተማሪዎች ሬጅስትራር ቢሮን ኮምፒውተራይዝድ የሆነ የመረጃ አያያዝ ለማድረግ ወደ ትግበራ ተገብቷል።

በገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የተማሪዎች ሬጅስትራር ቢሮን ኮምፒውተራይዝድ የሆነ የመረጃ አያያዝ ለማድረግ ወደ ትግበራ ተገብቷል።
ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም /ገ.ግ.ቴ.ሙ.ሥ.ኮ/
…………………………………………………….

የሬጅስትራር ቢሮ ሀላፊ አቶ ያሬድ ብርሀን እንዳብራሩት ፦
✅ የተማሪዎች ሬጅስትራር ቢሮችንን ዲጂታላይዝ ማድረጋችን የተማሪ መረጃዎችን በቀላሉና ፈጣን በሆነ መልኩ እንድናገኝ ያግዘናል፡፡

✅ በመሆኑም አንድ ተቋም ይህን አሰራር ጀመረ ማለት ወቅታዊ የቴክኖሎጅ አጠቃቀምን ከመጀመሩም ባሻገር በተቋሙ ያሉ መረጃዎችን በቀላሉና በፍጥነት ማግኘትና ለመረጃ ፈላጊው ማድረስ ይችላል ፡፡

✅ የተማሪዎችን የCOC ፎርማቱን በመከተል COC የሚመዘግብ፣ የሚተነትን ሲስተም ነው።

✅ አንድ ሰልጣኝ /ተማሪ/ መቼ እንደሰለጠነ፣ መቼ እንደተመረቀና ምንምን የብቃት አሃዶችን እንደወሰደ፣ በምን ሙያ እንደተመረቀ፣ የሰልጣኝ ቅጅ እና የማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ያዘጋጃል፡፡ እነዚህን ሁሉ መረጃዎችም በአንድ ጊዜ ፕሪንት አድርጎ መስጠትም ይችላል፡፡ አንድ ሰልጣኝ የራሱን መረጃ ማየት ከፈለገም  ሲስተሙን ተጠቅሞ በሞባይሉ ወይም በኮምፒውተር ሙሉ መረጃውን  ማየት ይችላል፡፡ መረጃው በሎካል ኤሪያ ኔትወርክ (LAN) የተያያዘ ስለሆነ ሁሉም የሬጀስትራር ባለሙያዎችም በቀላሉ መረጃዎችን መለዋወጥ ይችላሉ፡፡

✅ ይህ ቴክኖሎጅ ከሌሎች ዳታ ቤዝ ሲስተሞች ልዩ የሚያደርገው በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ለተጠቃሚዎች ምቹና ቀላል ሲሆን ደግሞ አይበለውና መረጃዎች በሰውሰራሽና ተፈጥራዊ አደጋዎች እንደ እሳት፣ ውሃና ጦርነት ባሉ አደጋዎች መረጃዎች ቢወድሙ በየቀኑና በየሰአቱ ቀጅ(backup) ወደ ጎጉል ድራይቭ ላይ መጫን(upload) ማድረግ ሲለሚቻል  መረጃዎችን እንደገና ማግኘት ሰለሚቻል ምንም አይነት ስጋት ሊኖር አይችልም፡፡

✅ በአጠቃላይ ይህ ቴክኖሎጅ የኮሌጁን ስታንዳርድ ከፋ ከማድረጉም ባሻገር የወረቀትን አሰራር የነበረውን የመረጃ አያያዝ ስርአታችንን ኮምፒውተራይዝድ በማድረግ አያያዙን ዲጂታላይዝ ያደረገ ቴክኖሎጅ ነው በማለት ፡፡

በመጨረሻም አቶ ያሬድ ብርሀን አክለውም በኮሌጃችን የ3ቀን ስልጠና ሲስተሙን በሰራው የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ ባለሙያ በመሰጠት ሲስተሙን ወደ ኮምፒዩተራቸው በመስጫን ወደ ተግበር የገቡ መሆናቸውን አበስረውናል ።
✍️✍️✍️  የኮሌጁ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *