የገዋኔ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ ኮሌጅ ከቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ጋር የጋራ ስምምነት አደረጉ።
ህዳር 13 ቀን 2015 ዓ.ም /ገ.ግ.ቴ.ሙ.ኮ/
……………………………………………………………
የተከበሩ የኮሌጁ ዲን አቶ መሀመድ ሀመዱ እንደገለፁት ይህ አጭር ስልጠና አሁን ኮሌጃችን በአዲሱ የስራና ክህሎት ሚኒስተር ከተሰጠን የትኩረት አቅጣጫ ወጣቶችን በአጫጭር ስልጠና ብቁ ማድረግና በማህበር በማደራጀት የራሳቸውን የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ ማድረግ ሲሆን አሁን ከምንሰጠው ስልጠና ጋር በቀጥታ ተዛማች የሆነና ለሰልጣኞች የምንሰጣቸው ስልጠና ከሌሎች የተሻሉ እና ሞዴል ማህበራት ሆነው እንዲበቁ እንዲሁም በተሰማሩበት አካባቢ ከሰለጠኑ ቡሀላም ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ለራሳቸው የስራ እድልን ፈጥረው እና ለማህበረሰቦቻቸው አርአያ ሆነው ለሀገራቸው የሚጠቅሙ ዜጋን ለመፍጠር ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል ።
እንዲሁም የተከበሩ አቶ ደርሳ አሊ በአፈር ክልል የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ እንደገለፁት ቀደም ሲል ፕሮጀክታችን ከኮሌጁ ጋር በመተባበር በኮሌጁ በተሰጡ ስልጠናዎች አመርቂ ውጤት በማምጣቱ በቀጣይ ይህን የጋራ ስምምነት ስንፈራረም በቆላማ አካባቢ የሚገኙ አርብቶ አደር ማህበረሰብ ኑሮን ለማሻሻል እና ለወጣቶች የስራ እድልን ለመፍጠር ከኮሌጁ ጋር በጋራ ለመስራት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርልናል ብለን በማመን በብር 2.8 ሚሊየን ድጋፍ የተያዘ ፕሮጀክት ከኮሌጁ ጋር የተደረገ ስምምነት ነው ።
በመጨረሻም የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮችና የፕሮጀክት አስፈፃሚ ሀላፊዎች በተደረገው የጋራ ስምምነት የተደሰቱ መሆናቸውን በመግለፅ ፍፃሜው የስምምነት ሰነዶች ላይ በመፈራረም የጋራ ስምምነቱ ተፈፅሟል ።
የኮሌጁ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዪች ዳይሬክቶሬት