የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር መሀመድ ኡስማን እና ሉኡካን ቡድኑ ከገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ጋር ዉይይት ተካሄደ።
መስከረም 10 ቀን 2015 ዓ.ም (ገ.ግ.ቴ.ሙ.ኮ)
በዛሬው ዕለት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የተከበሩ ዶ/ር መሀመድ ኡስማን ከነ ሉኡካን ቡድኑ በገዋኔ ግብርና ኮሌጅ በመገኘት ከኮሌጁ ዲን ክቡር አቶ መሀመድ ሀመዱ እንዲሁም የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች በተካፈሉበት መድረክ በመማር ማስተማር፣በማህበረሰብ አገልግሎት ፣ በቴክኖሎጂ ማሸጋገር እና በተለያዩ መሰል ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ ።
ክቡር ፕሬዚዳንቱ ከውይይቱ በፊት በኮሌጁ ከሉኡካን ቡድናቸው ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን ያሳርፉና እንዲሁም የኮሌጁ ነርሰሪ ሳይት እና ኮሌጁ በክረምት መርሀ ግብር አቅዶ በኮሌጁ ዙሪያ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ማህበረሰብ የመኖሪያ ቤት አፍርሶ መስራት ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን በጉብኝቱም ፕሬዚዳንቱ የተሰማቸውን ወደር የሌለው ደስታ ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በዋነኝነት በውይይቱ ከተነሱ ስምምነት ከተደረገባቸው ነጥቦች መካከል :-
- ለኮሌጁ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ከዲግሪ እስከ ፒኤችዲ ድረስ የነፃ የት/ት እድል እንደሚያመቻቹ።
- የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የኤክስቴንሽን ት/ት መርሀ ግብር በኮሌጁ እንዲሰጥ መወሰናቸው
- ዩኒቨርሲቲው ዱብቲ ከያዘው 40 ሄክታር መሬት ላይ ቋሚ ተክል ማለትም የተመረጠ ዝርያ ያለው የእስራኤል ቴምር ለመትከል በያዘው እቅድ ላይ ፕሬዚዳንቱ በኮሌጃችን ባዩት ምርጥ ተሞክሮ ከኮሌጃችን ባለሙያዎች ተወጣጥቶ የዚሁ ፕሮጀክት ተሳታፊ እንዲሆኑ መደረጉ።
- ከኮሌጃችን አሁን እያከናወነ ከሚገኘው በተጨማሪ በተለያዩ ቦታዎች የችግኝ ጣቢያውን ለማስፍፍት ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ ቃል መገባቱ።
- ኮሌጃችን በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አማካኝነት በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ካሉ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማትና ድርጅቶች ጋር ግንኙነት/ link / እንደሚፈጥሩልን ቃል መገባቱ። ወዘተ ናቸው።
በመጨረሻም የኮሌጁ ዲን የተከበሩ አቶ መሀመድ ሀመዱ ክቡር ፕሬዝዳንቱን ውድ ጊዜያቸውን ሰጥተው እዚህ ድረስ በመገኘታቸው ያላቸውን አክብሮትና ምስጋና ካቀረቡ ቡሀላ በቀጣይ ከዩኒቨርስቲው ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት እንደሚያደርጉ እና በመተባበር በተግባር እንደሚሰሩ በውይይቱ መቋጫ ገልፀዋል።
✍✍✍✍✍ አቶ ሙራድ ሱሌይማን
ከኮሌጁ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት