Background

  1. የገዋኔ ግብርና /ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ዳራ ( አጭር መግለጫ )

       የገዋኔ ግብርና ኮሌጅ ከዛሬ 53 ዓመታት በፊት በአፋር ክልል በገቢ ረሱ ዞን ገዋኔ ወረዳ ከአዲሰ አበባ ወደ ጅቡቲ በሚወስደዉ ጎዳና ላይ 350 ኪሎሜትርና ክክልሉ ዋና ከተማ ሰመራ በ220 ኪሜትር ርቀት ላይ ከባህር ጠለል በላይ በ560 ሚሜ ከፍታ የሚገኝ ሲሆን፣ኮሌጁ በምስራቅ የአዘሎ ትራራ ሰንሰለት፣ በሰሜን የቢሪፎሮ ቀበሌ፣ በማዕራብ የአዋሽ ወንዝ፣ በደቡብ የሙክቲደላ ቀበሌ ያዋስኑታል፣ 

       ኮሌጁ በ1962 ዓ.ም በአሜሪካን የሠላም ጓድ አባላት እና በወቅቱ የአካባቢው የአርብቶ አደር ጎሣ መሪዎች ይሁንታ ተችሮት የገዋኔ እንስሳት አርቢዎች ማሰልጠና ማእከል በሚል ስያሜ የተቋቋመ ሲሆን ዋነኛ አላማዉም ኑሮውን ዘመናዊ ባልሆነው የእንስሳት እርባታ ላይ የመስረተውን የአካባበዉ አርብቶ አደር እና ከአብራኩ የወጡ ልጆቹን በልዩ ልዩ የአጭርና የረዥም ግዜ ቆይታ ባላቸው የግብርና ሙያ መስኮች በማሰልጠን የሀብቱና የልማቱ ተጠቃሚ ሆኖ የኑሮ ደረጃውን ለማሻሻል ነዉ፡፡

  ተቋሙን የመሰረቱት የሰላም ጋድ አባላት በወቅቱ በተከሰተዉ ህዝባዊ ለዉጥ ሳቢያ ሀገራችንን ለቀዉ እንዲወጡ ሲደረግ የተለየዩ መስሪያቤቶች ስር እየተዳደረ የማህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎና የባለቤትነት መንፈስ ሳይለየዉ እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ የመጀመሪያ ደረጃ የቀለም ት/ትን አካቶ

  • በእንስሳት እርባታና የግጦሽ መሬት አያያዝና የመኖ ልማት!
  • በመስኖ አጠቃቀምና ሰብል ልማት!
  • በእንስሳት ጤና የቬት እስካዉት
  • የዱር እንስሳት እስካዉት

የሙያ መስኮች ከ1 ወር እስከ 3 ወር በሚደርስ የሥልጠና ቆይታ 1500 ያህል አርብቶ አደሮችን አሰልጥኖአል፡፡

ከ1985 እስከ 1993 ዓ.ም

ተጠሪነቱ ለአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ሆኖ ከክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች የተመለመሉ ወጣቶችን የዘጠኝ ወራት ቆይታ ያላቸዉ

  • በሁለገብ እርሻ
  • የረዳት እንስሳት ጤና ቴክኒሺያን

የሙያ መስክ 457 የልማት ወኪሎችን (DA’s) አፍርቶአል ፡፡

  • 1994 ዓ.ም እስከ 2013 ዓ.ም
    • የረዥም ግዜ ስልጠና

ተጠሪነቱ በግብርና ሚኒስቴር ለግብርና ሙያ ስልጠና ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ሆኖ መንግስት በቀየሰዉ አዲሱ የት/ትና ሥልጠና ፖሊሲ መሠረት በማድረግ ውስጣዊ   አደረጃጀቱንና የቅበላ አቅሙን በኮሌጁ ደረጃ አሳድጎ በ10+3 መደበኛ የት/ት መርሃ ግብር በሶስት ፕሮግራሞች (በእንስሳት ሳይንስ፣በእፅዋት ሳይንስና በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና ልማት) ሙያ መስኮች ግብአት ተኮርና ሞጁላራይዝድ በሆነ የስልጠና መርሃ ግብር ከሁሉም የአገራችን አካባቢዎች ተመልምለዉ የሚላኩለትን ወጣቶች ተቀብሎ በማሰልጠን በቁጥር        የመካከለኛ ደረጃ የግብርና ሙያተኞችን በማፍራት በግብርናው ዘርፍ ለተመዘገበዉ እድገት የበኩሉን ሀገራዊ ድርሻ ተወጥቶአል በመወጣት ላይም ይገኛል፡፡

  • መደበኛ ያልሆነ ስልጠና

የግብርና ሙያ ስልጠናን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ከክልሉ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ፣ከአፋር የቆላማ አካባቢ ኑሮ መሻሻል ፕሮጀክትና ከ GIZ SDR ጋር በመተባበር ለወረዳ የግብርና ልማት ሙያተኞች፣የገጠር ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሮች እንደ ፕሮግራሙ ይዘት ከ15-30 ቀን በሚደርስ ቆይታ በቁጥር ……….

  • በእንስሳት ማድለብና የወተት ላሞች እርባታ
  • በእንስሳት መኖ ልማት
  • በአነስተኛ የመስኖ ልማት
  • በአትክልትና ፍራፍሬ አመራረት
  • በአፈርና ዉሃ ጥበቃ (Watere spreding weer technology፣ Masonry and ፣ Dry stone measures  ላይ ያተኮረ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
  •  
  1. 40 + 66 + ወጣቶች
  2. ቴክኖሎጂ ሽግግር

ከሰዉ ሃይል ስልጠና በተጓዳኝ በተቋሙ አካባቢ የሚገኙ አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሮችን የልማት ማነቆ የሚፈታ ዉጤታማ ቴክኖሎጂ በማሸጋገር የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት የሆነውን የግብርና የምርታማነት ደረጃዉን በእጥፍ ለማሳደግ የተጣለበትን ተልእኮ ለመወጣት የተለያዩ የአትክልትና ፍራፍሬ፣የመኖ እጽዋቶችና የእንስሳት ዝርያዎችን ለአካባቢዉ ማህበረሰብ ከማሸጋገሩም በላይ

በተደጋጋሚ የድርቅ ተጠቂና ተጋላጭ በሆነው የክልላችን አርብቶ አደር  አካባቢ የተጎዱ የግጦሽ  መሬቶችን መልሰዉ እንዲያገግሙ የሚረዳ የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ስራዎች የማስተዋወቅ የቴክኖሎጂ ሽግግር በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻዎችና የልማት አጋሮች ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት የአደጋ ተጋላጭነት ሥጋትን ለመቀነስ የጎላ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡