- ቴክኖሎጂ ሽግግር
ከሰዉ ሃይል ስልጠና በተጓዳኝ በተቋሙ አካባቢ የሚገኙ አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሮችን የልማት ማነቆ የሚፈታ ዉጤታማ ቴክኖሎጂ በማሸጋገር የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት የሆነውን የግብርና የምርታማነት ደረጃዉን በእጥፍ ለማሳደግ የተጣለበትን ተልእኮ ለመወጣት የተለያዩ የአትክልትና ፍራፍሬ፣የመኖ እጽዋቶችና የእንስሳት ዝርያዎችን ለአካባቢዉ ማህበረሰብ ከማሸጋገሩም በላይ በተደጋጋሚ የድርቅ ተጠቂና ተጋላጭ በሆነው የክልላችን አርብቶ አደር አካባቢ የተጎዱ የግጦሽ መሬቶችን መልሰዉ እንዲያገግሙ የሚረዳ የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ስራዎች የማስተዋወቅ የቴክኖሎጂ ሽግግር በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻዎችና የልማት አጋሮች ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት የአደጋ ተጋላጭነት ሥጋትን ለመቀነስ የጎላ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡